Home Uncategorized መግለጫው አዲስ ነገር አላመጣም” አቶ ተሾመ ተ/ሃዋሪያት (የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ)

መግለጫው አዲስ ነገር አላመጣም” አቶ ተሾመ ተ/ሃዋሪያት (የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ)

SHARE

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ፣ ከ17 ቀናት በላይ የሀገሪቱን ችግሮች ገምግሞ፣ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያደረገው ስብሰባና በመግለጫው ላይ የተንፀባረቀው፣ ከተጠበቀው አንፃር፣ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ የሀገሪቱን ችግር በቅጡ ያየና የተገነዘበ አይደለም፡፡ የመግለጫውን ይዘት ላየ፣ አንዳንድ ተስፋ የሚፈነጥቁ ነጥቦች ቢኖሩትም፣ በተለይ በዲሞክራሲያዊ መብቶች አከባበር፣ በመድብለ ፓርቲ ስርአት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ረገድ ጠንካራ አቋም አልተንፀባረቀም። በ2008 ዓ.ም በጥልቀት ታድሰናል ተብሎ ከተሰጠው መግለጫ ብዙም የተለየ አይደለም፡፡ አንድም አዲስ ነገር ይዞ አልመጣም፡፡ ፕሬዚዳንቱ በ2009 ዓ.ም በፓርላማው ያደረጉት ንግግር ነበር፤ ያንን ንግግር እንኳ ገዥው ፓርቲ በቅጡ መሬት ማስረገጥ ያልቻለ ነው፡፡

ከ17 ቀናት ስብሰባና ሀገሪቱ በቋፍ ላይ ባለችበት ወቅት፣ ይህ የተለመደ መግለጫ መውጣቱ፣ ወደ መፍትሄው አያደርሰንም፡፡ ለደረሰው ነገር በሙሉ ሥራ አስፈፃሚው ሃላፊነት እንደሚወስድ ከተገለጸ በኋላ ድርጅቶቹ ተገማግመው እርምጃ ይወስዳሉ ይላል፡፡ ይሄ የተምታታ ነገር ነው፡፡ አንዴ ሥራ አስፈፃሚው ኃላፊነት ወስዶ ይቅርታ ካለ በኋላ፣ ከብሄራዊ ድርጅቶች የምን የግምገማ ውጤት ነው የሚጠበቀው? በመድብለ ፓርቲ፣ በሲቪክ ሶሳይቲ ረገድ በመግለጫው የተጠቀሰው ወደ ተግባር የሚለወጥ ከሆነ መልካም ነው፡፡ በሚዲያው በኩል ግን ማስፈራሪያ ውስጥ ነው የተገባው፡፡ ይሄ መጪውን ጊዜ ለሚዲያው ፈታኝ ሊያደርገው ይችላል፡፡

መግለጫው አዲስ ነገር አላመጣም” አቶ ተሾመ ተ/ሃዋሪያት (የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here