Home Uncategorized ‘በኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በሪዞርቱ ውስጥ የነበረው ንብረት ሙሉ በሙሉ...

‘በኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በሪዞርቱ ውስጥ የነበረው ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል’ – ፖሊስ | ዝርዝርሩን ያንብቡት …

SHARE

በአዳማ ከተማ እሬቻ ቀበሌ በሚገኘው ኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ የደረሰ የእሳት ቃጠሎ አዳጋ በንብረት ላይ ጉዳት ማስከተሉን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ትናንት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተኩል አካባቢ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በሪዞርቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በሪዞርቱ ውስጥ የነበረው ንብረት ሙሉ በሙሉ መውደሙን ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልጸዋል።

ከሁለት ሰዓት በላይ የፈጀውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ የፖሊስ አባላት ከፍተኛ ርብርብ በማድረጋቸው እሳቱ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

በተጨማሪም አደጋውን ለመቆጣጠር ከሞጆ ደረቅ ወደብ፣ ከቢሾፍቱ አየር ኃይል፣ ከትራክተር ፋብሪካና የከተማው መስተዳድር የእሳትና አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን ምክትል ኢኒስፔክተር ወርቅነሽ አስረድተዋል።

አደጋው በአካባቢው የነበረው ትራንስፎርመር ፈንድቶ የኤሌክትሪክ ኬብል በሳር ቤቶች ላይ በመውደቁ የተነሳ የተከሰተ መሆኑንም ገልጸዋል።

በቃጠሎው የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳይ ለማወቅ ኮማንድ ፖስት፣ ፖሊስና የሪዞርቱ ባለቤት በማጣራት ላይ መሆናቸውንም ተመልክቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here