Home Uncategorized በደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

SHARE

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አደጋው የደረሰው የህዝብ ማመላለሻ ሃገር አቋራጭ አውቶብስ 65 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ በመጓዝ ላይ እንዳለ ተገልብጦ ነው፡፡

የወረዳው ፖሊስ የትራፊክ መርማሪ ኢንስፔክተር ፍቅሩ ከበደ እንደገለጹት፥ ከአዲስ አበባ በ90 ኪሎ ሜተር ርቀት ላይ በተለምዶ ቃሲም ቀበሌ ገበሬ ማህበር አካባቢ

በደረሰው በዚህ አደጋ ህይወታቸው ካለፈው ሌላ 20 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፍቼ እና አዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ የጤና ተቋማት የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን የአደጋው መንስኤም እየተጣራ ነው ተብሏል።

ህይወታቸው ካለፈው መካከል አሽከርካሪውና አንድ የውጭ ዜጋ ሴት የሚገኙበት ሲሆን፥ አስክሬናቸውን ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

Fana

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here